የ “Lideta School Alumni Association” በተመለከተ
ክፍል ሁለት፤ ተጨማሪ አስተያየት
ክፍል አንድን “Concerning: Lideta School Alumni Association” የሚል የኢንግሊዝኛ ጽሑፍ ይመልከቱ።
አብዛኛው የኢሮብ ወጣት ለልማት እጁን ለመዘርጋት ዝግጁ መሆኑን እያረጋገጠ ነው።
አሁን ጅማሮው በልደታ ማርያም ትምህርት ቤት ላይ ያቶከረ ቢሆንም ቀጣይነት ያለው ተነሳሽነት መሆኑ ያመልክታል።
ይህንን የተቀደሰ ሓሳብ ተግባረዊ ለማድረግ ሁለት መሰረታዊ ነገሮች በትዩይ መቅደም አለባቸው።
አንደኛ
1. የትምህርት ቤቱ (የልደታ) ርእሰመምህር በጣምራ የሚያዙት የሂሳብ ቁጥር በቀድሚያ መከፈት አለበት
ይህም አቶ ሙዑዝ ፍሱሕ
Meuz Fessuh
18. august 14:34
hi guys:
i have contacted aba habtegebriel the director of lideta secondary school.he said he is has prepared the articles and memorandum of association,and that he will open an account in a weeks time together with committee in mekele.
በገለጹልን መሰረት በቅርቡ ተግባራዊ እንደሚሆን ተስፋችን የጸና ነው።
2. ለመርዳት የተነሳሳ ሁሉ በግሉ በመንቀሳቀስ የፈቀደውን ገንዘብ በቀጥታ ወደ ሂሳብ ቁጥሩ ማስገባት ይችላል
3. በያለበት አከባቢ በቡድ በመንቀሳቀስና በፈለገውና በፈቀደው አላማ ማለት
• መጸህፍትና የትምህርት መሳሪያ ማደራጃ ቡድን
• በኮምፒዩተርና ያዲስ ቶክኒዮሎጂ ግኝቶች ማደራጃ ቡድን
• በባህልና ትያተር ማደራጃ ቡድን
• በታሪክን ስነምርምር ጥናት
• በመምህራን ደሞዝና መደጎሚያ ማጠናከርያ መዋጮ
• ተማሪዎችን በምግብ ለመደጎም የሚንቀሳቀስ ቡድን እንዲሁም ወዘተ
በቡድን መደረጀት የፈለጉ ደግሞ በአከባቢያቸው በተስማሙበት መልኩ የራሳቸው ሂሳብ ቁጥር ከፍተው በመንቀሳቀስ ብርን ካሰባሰቡ በኋላ ለኢሮብ ህዝብ ይጠቅማል ሲሉ በተስማሙበት መልክ ወጪ እንዲሆን በማመላከት ብሩን በቀጥታ በልደታ ርእሰመምህር ጣምራነት በተከፈተው ሂሳብ መግባት አለበት።
እያንዳንዱ በፈቃደኝነትና በራሱ አነሳሽት የተደራጀው ቡድን ሂሳቡን ለትምህርትቡቱ ሂሳብ ቁጥር መላኩን ለኢሮብ ተወላጆች ሁሉ ማሳወቅ አለበት።
የትምህርት ቤቱ ርእሰመምህርና አብረውት በጣምራነት የሚሰሩ የኮሚቶው አባላት ደግሞ የስራ አፈጻጸምን ዝርዝር መግለጫ በሳይበር በእንተርነት በኩል በተለየዩ አህጉራት ተበትነን ለምንገኝ የኢሮብ ልጄች እንዲያበስሩ የግድ ይላቸዋል።
የልማት ተሳታፊዎቹ የኢሮብ አባላት ያዋጡተ ብር በአግባቡ በጥቅም ላይ መዋሉን ሲያረጋግጡ እርካታቸው ለበለጠ ተሳታፊነት ይጋብዛቸውና ሞተሩ እንደታደሰለት ባቡር፤ የልማት እንቅስቃሶአቸው ፍጥነት እንዲጨምር ይሆናል። ይህም ጥረታችን በአንድነት አጣምረን ተጣምረን፤ በቡድን ቡድን ከመደራጀት አልፈን፤ አቶ አለማ ተስፋይ ከዚህ ቀጥሎ “Lideta School Alumni Association” ሲሉ እንዳቀረቡት ፤
Alema Tesfaye
16. august 01:53
Dear Haileselasie Yohannes, I am very happy to see your wonderful and constructive comments on how to proceed once the organization is established and set on the right track. The steps that you proposed to go forward with this nobel idea of Lideta school alumni formation are appreciable. You also stated “I am assuming that this association is established by the current Director of Lideta Mariam School of Alitena (who have long ago have shared me his honorable idea) and I believe we have to be accountable to the school administration and not any other organ.” This statement is completely new for me. To get more evidence of it, I tried to call back home and ask about it and the people whom I contacted back home told me that they never heard about any association which is established.
Secondly, you stated in your above post “Under the umbrella of the Lideta School Alumni Association we can organize ourselves; say for example;
1. The book donor’s group
2. Computer donor’s group
3. “Best Teachers” financing group
4. Irob - cultural group
5. Irob-History group
6. “Water and food for the students” organizing group “.
This is very important comment that leads us well to hit our target after the association is established. I believe and stand firmly on it. But first of all, we have to establish the Alumni association of our historic Lideta School. It doesn’t matter who created it as we are just fighting for Irob people’s life improvement which focused on enlightening the future of our beloved Irobs back home.
Fugi niada yakoy.
ይሁን ወይስ እኔ ከወቅቱ የልደታ ርእሰመምህር በመጋቢት ወር 2003 ዓ.ም ጥንስሱን ብቻ ሳይሆን አንዴት መተግበር ይችላል ሲሉ ተጨንቀውና ተጠበው መላዎችን ሲዳስሱ እነደሰማሁት ይሁን ወይስ ሌላ አደስ አወቃቀር ወዘተ ለማደራጀትና ለማወቀር እንችላለን።ይህም ክፍል ሁለትን የጋብዛል።
ሁለተኛ
ክፍል ሁለት ከክፍል አንድ ጎን ለጎን የሚካሄድ የውይይት ድርጊት ነው። ይህም ሂደት ነው። በአንድ ዠንበር የሚሆን ስላልሆነ ቀስ በቀስ እየተወያየን በሰከነና በረጋ መንፈስ በውይይት አሁን በምናደረገው በሳይበር ዓለም ሃሳብ ለሃሳብ ልብ ለልብ በመለዋወጥና በማብሰል የሚደረስ ይሆናል። ስለዚህ አሁን በተጀመረው በሳል አካሄድ ምክክረችንን እንቀጥል።
ወንድሜ አለማ ተስፋይ አንዳለው ፤ሃሳቡን ማንም ያፍልቀው ማንም ዋናው ቁምነገር የዚህ የተቀደሰ አላማ ግብ መምታት ጅማሮና ውጤት መጨበጣችንና ማየታችን ነው።
ላረጀው ላፈጀው መንፈስን የሚያውደው፡
አዲሱ ትውልዳችን የለውጥ መዘውር ነው።
የኢሮብ ወጣቱ ትውልድ በረቱ ተበራቱ
በጠባቡ ሳይሆን በሰፊው አትቱ
በጥላቻ ሳይሆን በፍቅር ወትውቱ
የዛሮውኑ ሳይሆን የጥንቱን ተመልከቱ።
አጻጻፍ አነጋገር አሳምሩ!
ሌላውን ለማስገደድ አትዳክሩ!
በፍቅር በሃሴት ተከባበሩ!
ከልብ በመንፈስ ተማከሩ!
ተደጋገፉ ተግባቡ እንጂ አትጎነታተሉ
ተዋደዱ ተከባበሩ እንጂ አትወነጃጀሉ
አጻጻፍ አነጋገር አሳምሩ!
ሌላውን ለማስገደድ አትዳክሩ!
በፍቅር በሃሴት ተከባበሩ!
ከልብ በመንፈስ ተማከሩ!
በወንድማቹህ ላይ ቀንበርን አትጫኑ
የሰማችሁትን ሁሉ በደረቁ አትመኑ
ማንበብና ማመሳከርን ልመዱ
አሉባልታንና ቡድናዊነትን አስወግዱ
ሀገራዊነትንና ህዝባዊነትን ገምዱ
ኢሮባዊነትንና ወገናዊነት አወድዱ
ሞዶይሳ
Visitor IP: 84.215.244.123
No comments:
Post a Comment